አዘጋጅ፦ ዲያቆን ንጋቱ አበበ
መልካም ትምህርትን እሰጣችኋለሁና ሕጌን አትተዉ። መጽሐፈ ምሳሌ 4፤2
መጽሐፍ
ቅዱስ ማለት ምን ማለት ነው?
v መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው ሐረግ መጽሐፍ እና ቅዱስ ከሚለው ሁለት ቃላት የተገኘ ነው።
v መጽሐፍ የሚለው
ቃል ተጠቃሎ በአንድ ጥራዝ ሥር የተሰበሰበ ጽሑፍን ሲገልጥ
v ቅዱስ የሚለው
ቃል በዕብራይስጥ “ከዳሽ” በሱርስት “ካዲሽ” በግእዝ እና በአረብኛ “ቅዱስ” ካለው ቃል የተገኘ ነው ትርጉሙም የተለየ ማለት ነው።
v መጽሐፍ ቅዱስ
ማለት በአንድ ጥራዝ ሥር የተሰባሰበ የተለየ ጽሑፍ ማለት ነው።
v መጽሐፍ ቅዱስ ማለት የተለየ፤ የተከበረ፤ የተቀደሰ ማለት ነው።
መጽሐፍ
ቅዱሳዊ ማስረጃ
Ø የተለየ
Ø የተከበረ
በቅዱሳን ምክር እግዚአብሔር ክቡር ነው በዙሪያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላቅና ግሩም ነው። መዝሙረ ዳዊት
89፤7
Ø የተቀደሰ
v የእግዚአብሔር የሆነ ሁሉ ቅዱስ ስለሆነ፤ አስገኚውም ራሱ ባለቤቱ (እግዚአብሔር) ስለሆነ ቅዱስ ተባለ።
መጽሐፍ
ቅዱሳዊ ማስረጃ
Ø እኔ እግዚአብሔር
አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ። ዘሌ 19፤2
Ø የጠራችሁ ቅዱስ
እንደሆነ እናንተም ደግሞ በኑሯችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ። 1ኛ ጴጥ 1፤15-16
v መጽሐፍ ቅዱስ
የሰውን ልጅ ደካማ ፍጥረት አንብቦ ተረድቶ አምኖ ተቀብሎ ወደ ተቀደሰ ሕይወት የሚያደርስ ስለሆነ ቅዱስ ተባለ።
Ø የዚህን መጽሐፍ
ትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብጹዕ ነው። ራዕ 2፤7
Ø በእግዚአብሔር መንፈስ የተነሳሱ ቅዱሳን ሰዎች የጻፉት በመሆኑ ቅዱስ ተባለ።
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ
ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ። 2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፥20
v የሰው ልጅ
ከመፈጠሩ በፊት ስላለው ሁኔታ በእርግጠኝነት ስለሚናገር
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ
Ø በመጀመሪያ እግዚአብሔር
ሰማይና ምድርን ፈጠረ። ዘፍ 1፤1
v ወደፊት ስለሚመጣው በእርግጠኝነት ስለሚናገር፤
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ
— ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።
እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።
v የሚያነቡትን እና የሚሰሙትን ስለሚባርክ፤
ሌሎች መጽሐፍትን በማንበብ ምክር እና እውቀት ይገኛል መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ እና በመስማት ግን ምክር፤ እውቀት፤ እንዲሁም ቡራኬ ይገኝበታል
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ
ራዕ 1፤3
v ዘመን የማይሽረው
በመሆኑ
Ø መጽሐፍ ቅዱስ
ዘመን የማይሽረው፤ የማያረጅ ዘላለማዊ ነው።
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ
Ø የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።
ኢሳ 40፤8
Ø ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም። ማቴ 24፤35
Ø የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል። በወንጌልም የተሰበከላችሁ ቃል ይህ ነው።
v ክብረ ቅዱሳንን
የሚዘክር በመሆኑ ቅዱስ ተባለ
ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፤ ስለ ቅዱሳን መላእክት፤ ስለ ቅዱሳን፤ ጻድቃን ሰማዕታት ሰለሚናገር ቅዱስ ተባለ።
ቃለ ሕይወት ያሰማልን
ReplyDelete