.

.
ዋና ገጽ » » የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት (ክፍል አንድ)

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት (ክፍል አንድ)

ዲያቆን ንጋቱ አበበUnknown ቤተልሔም ዘተዋሕዶ Saturday, February 21, 2015 | 9:19 AM


                                                            አዘጋጅ፦ ዲያቆን ንጋቱ አበበ
           መልካም ትምህርትን   እሰጣችኋለሁና ሕጌን አትተዉ።  መጽሐፈ   ምሳሌ 42
መጽሐፍ ቅዱስ ማለት ምን ማለት ነው?
v  መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው ሐረግ መጽሐፍ እና ቅዱስ ከሚለው ሁለት ቃላት የተገኘ ነው።
v   መጽሐፍ የሚለው ቃል ተጠቃሎ በአንድ ጥራዝ ሥር የተሰበሰበ ጽሑፍን ሲገልጥ
v   ቅዱስ የሚለው ቃል በዕብራይስጥከዳሽበሱርስትካዲሽበግእዝ እና በአረብኛቅዱስካለው ቃል የተገኘ ነው ትርጉሙም የተለየ ማለት ነው።
v   መጽሐፍ ቅዱስ ማለት በአንድ ጥራዝ ሥር የተሰባሰበ የተለየ ጽሑፍ ማለት ነው።
v  መጽሐፍ ቅዱስ ማለት የተለየ፤ የተከበረ፤ የተቀደሰ ማለት ነው።
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ
Ø                  የተለየ
እርሱም፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ አፍህ ይብላ፥ በምሰጥህም በዚህ መጽሐፍ ሆድህን ሙላ አለኝ። እኔም በላሁት፥ በአፌም ውስጥ እንደ ማር ጣፈጠ። ትንቢተ ሕዝቅኤል33
Ø                  የተከበረ
በቅዱሳን ምክር እግዚአብሔር ክቡር ነው በዙሪያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላቅና ግሩም ነው። መዝሙረ ዳዊት 897
Ø          የተቀደሰ
እኔ አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር ነኝ እንግዲህ እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ።  ዘሌ1145
v  የእግዚአብሔር የሆነ ሁሉ ቅዱስ ስለሆነ፤ አስገኚውም ራሱ ባለቤቱ (እግዚአብሔር) ስለሆነ ቅዱስ ተባለ።
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ
Ø    እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ። ዘሌ 192
Ø   የጠራችሁ ቅዱስ እንደሆነ እናንተም ደግሞ በኑሯችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ። 1 ጴጥ 115-16
v   መጽሐፍ ቅዱስ የሰውን ልጅ ደካማ ፍጥረት አንብቦ ተረድቶ አምኖ ተቀብሎ ወደ ተቀደሰ ሕይወት የሚያደርስ ስለሆነ ቅዱስ ተባለ።
Ø    የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብጹዕ ነው። ራዕ 27
Ø  በእግዚአብሔር መንፈስ የተነሳሱ ቅዱሳን ሰዎች የጻፉት በመሆኑ ቅዱስ ተባለ።
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ
ይህን በመጀመሪያ እወቁ፤ በመጽሐፍ ያለውን ትንቢት ሁሉ ማንም ለገዛ ራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም፤ ትንቢት ከቶ በሰው ፈቃድ አልመጣምና፥ ዳሩ ግን በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ። 2 የጴጥሮስ መልእክት 120
v   የሰው ልጅ ከመፈጠሩ በፊት ስላለው ሁኔታ በእርግጠኝነት ስለሚናገር
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ
Ø   በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ።  ዘፍ 11
v  ወደፊት ስለሚመጣው በእርግጠኝነት ስለሚናገር፤
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ
ትንቢተ ኢሳይያስ 714 (ስለሚመጣው በእርግጠኝነት የተናገረበት ክፍል)
  ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።
የማቴዎስ ወንጌል 123 (ትንቢቱ ሲፈጸም)
እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።
v  የሚያነቡትን እና የሚሰሙትን ስለሚባርክ፤
ሌሎች መጽሐፍትን በማንበብ ምክር እና እውቀት ይገኛል መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ እና በመስማት ግን ምክር፤ እውቀት፤ እንዲሁም ቡራኬ ይገኝበታል
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ
ራዕ 13
v   ዘመን የማይሽረው በመሆኑ
Ø   መጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የማይሽረው፤ የማያረጅ ዘላለማዊ ነው።
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ
Ø  የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች ኢሳ 408
Ø   ሰማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም ማቴ 2435
Ø  የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል። በወንጌልም የተሰበከላችሁ ቃል ይህ ነው።
1 የጴጥሮስ መልእክት125
v   ክብረ ቅዱሳንን የሚዘክር በመሆኑ ቅዱስ ተባለ
ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፤ ስለ ቅዱሳን መላእክት፤ ስለ ቅዱሳን፤ ጻድቃን ሰማዕታት ሰለሚናገር ቅዱስ ተባለ።

1 comments:

በሳምንት ጊዜ ውስጥ ብዙ የተነበቡ