.

.
ዋና ገጽ » » መግቢያ የቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ምንነት

መግቢያ የቤተክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ምንነት

ዲያቆን ንጋቱ አበበUnknown ቤተልሔም ዘተዋሕዶ Tuesday, February 17, 2015 | 10:43 PM


በዲያቆን ንጋቱ አበበ

የቤተ ክርስቲያን ታሪክና የዓለም ታሪክ አንድ ክፍል ነው።  አንድ የታሪክ ምሁር ታሪክን በሚያጠናበትና በሚመረምርበት ወቅት ብሎግ ልማስተማር በሚዘጋጅበት ጊዜ በየትኛውም ደረጃ ላሉ የታሪክ ትምህርት ዘርፍ ለሚማሩ ተማሪዎች የቤተክርስቲያንንና በአጠቃላይ የሃይማኖትን ታሪክ መንካቱ አይቀሬ ነው።  ምክንያቱም ለዓለም ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ሃይማኖት ወሳኝ ሚና ነበረው፤ አለው፤ ወደፊትም ይኖረዋል።  የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ከሌሎች የታሪክ ትምህርት ዘርፎች ለየት ብሎ የቤተ ክርስቲያንን አመሠራረት አድገትና አሁን ያለችበትን ሁኔታ  የሚያጠና አንድ የታሪክ ትምህርት ዘርፍ ነው።
አጠር ባለ መልኩ ብናስቀምጠው የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ትምህርት ማለት የክርስትና እምነት ታሪክ ትምህርት ማለት ነው።  የክርስትና እምነት ታሪክ ደግሞ የ እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ መለገጥ ነው።  በ  እርግጥ የ እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን ተዋህዶ ሰው ሆኖ ከምምጣቱ ቀደም ብሎ ቤተ ክርስቲያን የሚለው ጽንሰ ሃሳብ በይፋ አይኑር እንጂ ከዚህ በኋላ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ እንደምንመለከተው ቤተክርስቲያንን የሚወክሉና ለ እውነተኛይቱ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን እንደምሳሌ ያገለገሉ ክስተቶች እንደነበሩ እናያለን። 
እንግዲህ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ሲባል በጥቅሉ የሚዳስሳቸው ነጥቦች ቅድመ ፍጥረተ ዓለም ከነበረው ዓለመ መላእክት  (የቅዱሳን መላእክት ሕብረት)አንስቶ ቅድስት ቤተክርስቲያን አሁን እስካለችበት  ጊዜ ድረስ በምን ሁኔታ አለፈች? መቼ እንዴት ለምን? በእነማን? ምን አገኘች? ምንስ አጣች ይሆናሉ።

የቤተ ክርስቲያን የታሪክ ትርጓሜ
የቤተ ክርስቲያን ትርጓሜ
ቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል ትርጉሙ የክርስቲያኖች ቤት ማለት ሲሆን በምሥጢር ሲተነተን ደግሞ
·       ሕንጻው
·       ማህበረ ም ዕመናን (የምዕመናን ማህበር)
·       የእያንዳንዱ ክርስቲያን ሰውነት
ሕንጻው (የመጀመሪያው ትርጉም)፤
ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሲሰራ በሰማያዊት ኢየሩሳሌም አምሳል ነው የሚሰራው፤ እያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያን ሲሰራ አብረው የሚሰሩአ ሊቀሩ የማይችሉ አገልግሎት የሚሰጡ አሉ እነሱም
1.     ቤተልሔም፤                 ለቅዱስ ስጋውና ለክቡር ደሙ ማዘጋጃ የሚሆን ስንዴና ወይን ማኖሪያና ማዘጋጃ ቦታ) በስተምሥራቅ በኩል መታነጽ አለበት።
2.    ግብር ቤት፤          ከአገልግሎት በኋላ አገልጋዮች ተሰብስበው ምግብ የሚመገቡበት ቦታ ነው።
3.    ክርስትና ቤት፤      ወንዶች በተወለዱ በ40 ቀን፤ ሴቶች ደግሞ በተወለዱ በ80 ቀናቸው የሚጠቀሙበትና ስመ ክርስትናና ሃብተ ወልድ በካህኑ አማካኝነት የሚያገኙበት ቦታ ነው።
4.    ዕቃ ቤት፤    የተላያዩ የቤተ ክርስቲያን መገልገያ መሳሪያዎች የሚቀመጥበት ቦታ ነው።
5.    ደጀ ሰላም፤ ጠቅላላ ግቢውን ይመለከታል ኢሣ 56፤7 ኤር 7፤10 ማር 21፤13

ማህበረ ምዕመናን  (የምዕመናን ማህበር)
ይህ ስም የክርስቲያን ወገን ሁሉና ክርስቲያን የሆነ ሁሉ የሚጠራበት ሥም ነው። ክርስቲያኖች ቤተ ክርስቲያን ይባላሉ።  ቤተ ያዕቆብ፤ ቤተ አሮን ሲል የ እስራኤል፤ የያዕቆብ እና የአሮን ወገን እንደሆነ ሁሉ የክርስቲያኖች በአንድ ሕብረት ተሰብስበው ሲገኙ ያ እንድነታቸው ወይም ማህበራቸው ራሱ ቤተ ክርስቲያን ይባላሉ።  1ኛ ቆሮ 11፤18 እና 14፤19-35 ከያ ዕቆብ የተወለደ ሁሉ ቤተ እስራኤል እንደሚባሉ ሁሉ በመንፈሳዊ ምሥጢራዊ ልደት ከክርስቶስ የተወለዱ ምዕመናን ቤተ ክርስቲያን ይባላሉ። 1ኛ ቆሮ 11፤18 እና 12፤19-35 የሐዋ 18፤22 እና 20፤28)
በ እብራይስጥ ካሌዮ ካሎ በግሪክ አክሌሲያ ይባላል። ሰባው ሊቃውንት በ እብራይስጥ ካሌዮ ካሎ የሚለውን አክሌሲያ በሚለው የግሪክ ግስ ተክተው ተርጉመውታል።  አክሌሲያ ማለት በግሪክ ምርጦች ማለት ነው። ዘዳ 9፤10 ዘኁ 10፤13 እና 20፤41

እያንድንዱ ሰው
ማለትም እያንዳንዱ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ይባላል። ይኽውም ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ማደሪያ፤ የእግዚአብሔር ማደሪያ ሲሆን በምድርም ላይ ካሉት ፍጡራን ሁሉ ክቡር ፍጡር ስለሆነ ቤተ ክርስቲያን ይባላል። 1ኛ ቆሮ 3፤16 2ኛ ቆሮ 6፤16 ሮሜ 8፤9 ሐዋ 5፤11 12፤1 ዘሌ 26፤11 ዮሐ 14፤23

ቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል በብሉይ ኪዳን 96 ጊዜ ተጠቅሷል በሐዲስ ኪዳን ደግሞ 114 ጊዜ ተነስቷል ይኸውም
·       በማቴዎስ ወንጌል 3 ጊዜ
·       በቅዱስ ጳውሎስ መልዕክታት 63 ጊዜ
·       በሐዋርያት ሥራ 23 ጊዜ
·       በ3ኛ ዮሐንስ መልዕክት 3 ጊዜ
·       በቅዱስ ያዕቆብ መልዕክት 1 ጊዜ
·       በአንደኛ ቅዱስ ጴጥሮስ መልዕክት 1 ጊዜ
·       በራዕይ ዮሐንስ 20 ጊዜ ሲሆን
ያልተጠቀሰባቸው የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ደግሞ
·       የማርቆስ ወንጌል
·       የሉቃስ ወንጌል
·       የዮሐንስ ወንጌል
·       2ኛ ጢሞቴዎስ
·       ወደ ቲቶ
·       2ኛ ጴጥሮስ
·       1ኛ እና 2ኛ ዮሐንስ መልዕክት
·       የይሁዳ መልዕክት ናቸው።

ይቀጥላል………………

0 comments:

Post a Comment

በሳምንት ጊዜ ውስጥ ብዙ የተነበቡ